ምን አይነት አመጋገብ መከተል አለብኝ?

apples, basket, fruits

ጤናማ አመጋገብ ምን ማለት ነው?

ጤናማ አመጋገብ ማለት ከእያንዳንዱ የምግብ አይነት በየቀኑ መመገብ ማለት ነው፡፡

እንዴት የተመጣጠነ አመጋገብ መመገብ ይቻላል?

የተመጣጠነ አመጋገብ ለመመገብ አምስት የምግብ አይነቶችን፣ ከፍራፍሬ፣ እህል፣ ወተት እና የወተት ተዋፃኦ፣ አትክልት፣ እንዲሁም ፕሮቲን/ገንቢ ምግቦች አቀናጅቶ የእለት ምግብ ውስጥ ማካተት ያስፈልጋል።

አትክልት አትክልት በጥሬው ወይም በስሎ ሊበላ ይችላል፡፡ ሲበስል የተወሰነ ንጥረነገሩን ሊቀንስ ይችላል፡፡ የአትክልት ልጣጭ ለመፈጨት ሊክበድ ስለሚችል፣ ቲማቲም፣ ድንች እንዲሁም የተለያዩ አትክልቶችን ልጣጩን በማንሳት መጠቀም ይመከራል።  

ፍራፍሬ፡ ከጁስ በላይ ሙሉውን ፍራፍሬ መመገብ ይመከራል።

እህል፡ ያልተከካ ጥራጥሬ ከተከካው ይበልጥ ፋይበር አለው። እንደ ኦትስ/ኣጃ፣ ቡኒ ሩዝ የመሳሰሉትን ይምረጡ፡፡

ፕሮቲን/ገነቢ ምግብ ከምንበላው አንድ አራተኛው ፕሮቲን አዘል ምግብ መሆን አለበት። ጥሩ ምርጫዎች ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ፣ የአሳ ስጋ፣ እንዲሁም እንደ ባቄላ፣ አተር፣ ሽንብራ እና ለውዝ የመሳሰሉትን ምግብ ውስጥ ማካተት ያስፍለጋል።

የአንጀት ቁስለት በሰውነታችን ላይ የሚያስከትለው ጉዳት

አንጀት በአጭሩ ሶስት ስራዎችን ይሰራል፡፡

  1. የበላነውን ምግብ መፍጨት
  2. ከተፈጨው ምግብ ንጥረ ነገሮችን ወደሰውነት መቀበል
  3. አላስፈላጊ ነገሮችን ከሰውነታችን ውስጥ ማስወገድ

የአንጀት ቁስለት በሽታ የተለያዩ የአንጀት ክፍሎችን ያጠቃል። “ክሮንስ” ሕመም ከአፍ ጀምሮ እስከ ፊንጢጣ ሊያጠቃ የሚችል ሲሆን “አልሰሬቲቭ ኮላይተይስ” የትልቁን አንጀት ብቻ ያጠቃል። ስለዚህ እንደሕመሙ አይነት እንዲሁም እንደተጠቃው የአንጀት ክፍል አይነት የሚያስከትለውም የአንጀት ስራ መኋደል ይለያያል።

ትንሹ አንጀት ከተቆጣ የምንበላው ምግብ ወደ ሰውነታችን የመቀበል ችግር ሊኖር ይችላል።

ትልቁ አንጀት የሚጠቃ ከሆነ የወሰድነው ውሃ ሰውነታችን መቀበል ስለሚከብደው ለአጣዳፊ ተቅማጥ ይዳርጋል።

የአንጀት ቁስለት ለማቅለሽለሽ እንዲሁም ማስመለስ፣ የሆድ ቁርጠት፣ አንዳንዴ ደም የቀላቀለ ወይም ደም የሌለው ተቅማጥ፣ የምግብ ፍላጎት መቀነስ፣ የሆድ ድርቀት፣ ድካም እንዲሁም የክብደት መቀነስ ለአመጋገብ መስተኋጎል ይዳርጋል።

ከዚህ በተጨማሪ የማቅለሽለሽ ስሜት እና የሆድ ቁርጠት ለተጨማሪ ምግብ ፍላጎት መቀነስ ይዳርጋል። ተቅማጥ ሰውነታችን ውስጥ ያሉትን ንጥረ ነገሮች በፈሳሽ መልክ እናጣዋለን።

ከሰገራ ጋር አብሮ የሚወጣ ደም ካለ ከጊዜ በኋላ ለደም ማነስ ከመዳረግ በተጨማሪ የድካም ስሜትን ያባብሳል።.

intestines, bowel, guts
tea, drink, cup

የአንጀት ቁስለት እና መጠጦች

ፈሳሽ መጠጣት በተቅማጥ መልክ የሚወጣውን ውሃ ይተካልናል። ማዘውተር ያለብን ፈሳሶች ውሃ እንዲሁም የፍራፍሬ ጭማቄዎች ናቸው። እነዚህን ፈሳሶች በዝግታ መጠጣት አብሮ ሊገባ የሚችል አየርን በመቀነስ አላስፈላጊ የሆድ መወጠር ስሜቶችን መቀነስ ይቻላል። ተቅማጥ ከበዛ ORS አብሮ የወጡትን ንጥረ ነገሮች ለመተካት ይረዳል።

ከለስላሳ መጠጦች አብሮ ያለው ጋዝ ለሆድ መወጠር ይዳርጋል።

ቡና እና ሻይ የመሳሰሉት መጠጦች የአንጀት ግድግዳዎችን ስለሚያነቃቃ የበለጠ ለተቅማጥ ያጋልጣል። አልኮል አዘል መጠጦች ከመጠን ባለፈ መጠጣት እንዲሁ በተመሳሳይ መልኩ የአንጀት ቁስለት ማገርሸት ያመጣል።

የሆድ መወጠር አንዱ ምቾት የሚነሳ የበሽታው ባህሪ ሲሆን አንዳንድ ቀለል ባሉ መንገዶች መቀነስ ይቻላል።

  1. በአንድ ጊዜ ብዙ አለመብላት
  2. አንዳንድ ለእርሶ የማይስማማ ምግቦችን ለይቶ ማወቅ፣ ለምሳሌ፣ ወተት እና የወተት ተዋጻኦ/ ፍሬ የበዛባቸው እንደ ቲማቲም፣ ›››
  3. አየር አብሮ ላለመዋጥ መጠንቀቅ። ማስቲካ በማኘክ፣ በመምጠጫ መጠጣት፣ እንዲሁም ለስላሳ እና ሌሎች ጋዝ ያላቸው መጠጦች ባለመጠቀም።
  4. ውሃ መጠጣት እንዲሁም የሰውነት እንቅስቃሴ ማድረግ።